ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤትን ጎበኙ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ያደረጉት ጉብኝትም ከ46 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ መሪ ደረጃ የተደረገ ጉብኝት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ ባደረጉት ጉብኝት ጥንታዊ ስዕሎችን፣ ላቦራቶሪዎች እና ሌሎች የሥነ ጥበብ ውጤቶችን ተመልክተዋል።

ትምህርት ቤቱ የሀገሪቱን በሚመጥን መልኩ እንዴት መደራጀት እንደሚችልም ከመምህራኑ ጋር መወያየታቸውንም ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ የሚገኘውን ዞማ ቤተ መዘክርንም በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው እለት የጎበኙት ዞማ ቤተ መዘክር የቆሻሻ መጣያ የነበረውን ሥፍራ የአትክልትና የመዝናኛ ሥፍራ ተደርጎ መለወጡ እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመቀየር እንደ ዞማ መሥራቾች ችግርን አሸንፈው መሥራት አለባቸው ሲሉም  ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት