ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ቆይታ አደረጉ

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘጋጀ መርሃግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባላቸው እዉቀት እና ልምድ የጋራ ከተማችንን አዲስ አበባን ለመለወጥ የሚከናወኑ ስራዎችን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን ኑሯችሁን በአሜሪካ ብታደርጉም ዋና ከተማችሁ አዲስ አበባ ሃገራችሁ ደግሞ ኢትዮጵያ ናት ያሉት ኢንጂነር ታከለ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት መንፈስ ሃገራችንን ለመለወጥ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል።

በተለያዩ መስኮች አዲስ አበባ ላይ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን የሚያስተባብር ልዩ ቢሮ እንደሚቋቋም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ላደረጉላቸው አቀባበልም ምስጋና ማቅረባቸውን ተጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፡- ከንቲባ ፅህፈት ቤት