አቶ አባዱላ ገመዳ በልጃቸው ህይወት ላይ ተመርኩዘው የፃፉት መፅሃፍ ተመረቀ

የቀድሞ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ በልጃቸው ህይወት ላይ ተመርኩዘው የፃፉት መፅሃፍ ተመረቀ፡፡

በፖለቲካ ህይወታቸው እስከ ኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነትና የኢፌዴሪ አፈ-ጉባኤነት ያገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ የአዕምሮ እድገት ውስንነት በገጠማት ልጃቸው ህይወት ዙሪያ ያጠነጠነ መፅሃፋቸውን ነው ያስመረቁት፡፡

“ዲቦራ” በሚል ስያሜ የወጣውና በአራተኛ ልጃቸው ስምና ህይወት ላይ ያተኮረው መፅሃፋቸው፣ ስትወለድ ጀምሮ ከገጠማት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ማለትም Down syndrome ጀምሮ አሁን የደረሰችበትን የጤና ሁኔታ የሚያስቃኝ ነው፡፡

አቶ አባዱላ ሁለተኛ ስራቸው የሆነው ይህ መፅሃፍ ለህትመት የበቃበትም ዓላማ ልጃቸው ስትወለድ የገጠማትን የእዕምሮ ጤና ችግር በመቅረፍ ህይወቷን የተቃና ለማድረግ ቤተሰባቸው የሄደበትን መንገድ ሌሎች እንዲማሩበት በማሰብ ነው ተብሏል፡፡

ከ6 ልጆቻቸው 4ኛ ልጃቸው የሆነችው የ9 ዓመቷዲቦራ፣ አሁንላይ የ3ኛ ክፍል ተማሪ መሆኗም ተገልጿል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ አቶ አባዱላ ገመዳ እንዳሉት በሃገሪቱ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያላቸውን ልጆች ተገቢውን ህክምና በጊዜ የማግኘት ችግር እንዳለባቸው ያታወሱ ሲሆን በጊዜ ህክምና አለማግኘታቸው ደግሞ ቶሎ መፍትሄ እንዳያገኙ እያደረጋቸው ነው ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ በትኩረት ሊሰራበት ይባልም ብለዋል፡፡

ከመጽሃፉ ሽያጭ የተገኘው ገቢም የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ብሔራዊ ማኅበር ገቢእንደሚሆንምተናግረዋል፡፡

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስትር፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ብሔራዊ ማኅበርና አርቲስቶች በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡