ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ኢሞን ግሊሞርን አነጋገሩ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ኢሞን ግሊሞርን ዛሬ በብሄራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የዛሬ ሶስት ወራት አካባቢ ሃላፊነታቸውን የተረከቡት ኢሞን ግሊሞር ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጋር የነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በመሰረቱት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ያተኮረ እንደነበረ ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ህብረቱ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ስራዎችን እንደሚያደንቅና በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ልዩ መልዕክተኛው አረጋግጠዋል፡፡