ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች በፅዳት ዘመቻው ተሳትፈዋል።

በዚህ የፅደት ዘመቻ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ነዋሪዎች በፅዳት ዘመቻው ዘረኝነትን እጠየፋለሁ! አብሮነትን አከብራለሁ! ከተማዬንም አፀዳለሁ! እና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ተሳትፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ነዋሪዎች አዲስ አበቤነት አስተሳሰብና ፅዳት መሆኑን በተግባር አሳይተውናል በማለት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የምንወዳትን ከተማችንን በጋራ ለማፅዳት ዛሬ የተሳተፈችው ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው።

ምክትል ከንቲባው በምስጋና መልዕክታቸው ከተማን ማፅዳት ቤትን እና ራስን ማፅዳት እንደሆነ ሁላችን ተረዳድተን ከተማችንን ውብና ማራኪ በማድረግ ፅዳት ባህላችን እናደርጋለን ብለዋል።