ወደ ትምህርት በማይመለሱ የህክምና ተማሪዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ከዛሬ ጀምሮ ወደ ትምህርት በማይመለሱ የህክምና ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የመጨረሻ አመት ተማሪዎች እና ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እርምጃዎች እንደተወሰዱ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ምላሽ ላላገኙ ጥያቄዎችም በዝርዝር አጥንቶ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አራት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባታቸውም  ተገልጿል፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች መኖራቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ወደ ትምህር ገበታ አለመመለስ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ተማሪዎች ተገንዝበው በፍጥነት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ አሳስቧል፡፡