ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከውጭ አገር ዩኒቨርሲቲ ልዑካን ጋር ተወያዩ

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኔቨራስካ ከመጡ ልዑካን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ካለፈው አንድ አመት ወዲህ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስኮች ውጤታማ ሪፎርሞች እያከናወነች እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው ከሀገሪቱ የካቢኔ አባላት ቁጥር 50 በመቶ የሚሆነው በሴቶች እንዲያዝ መደረጉ እንዲሁም የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጭምር ሴቶች እንዲሆኑ መደረጋቸው ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ዩኒቨርሲቲዎቹ ለሰላም ሚኒስቴር የልምድ ልውውጥ መድረክ፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን ድጋፍ በማድረግ ሀገሪቱ የጀመረችውን የትራንስፎርሜሽ ጉዞ እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡

(የሰላም ሚኒስቴር)