ኢትዮጵያ አዲስ የተገኘውን ግዙፍ የህዋ አካል እንድትሰይም ተመረጠች

የዓለም አቀፉ የህዋ ህብረት አዲስ ለተግኘው ግዙፍ የህዋ አካል ኢትዮጵያ ስም እንድታወጣ እድሉን መስጠቱ ተገለጸ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ለአዲስ ለተገኘው ግዙፍ የህዋ አካል ዜጎች ስያሜ እንዲያወጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የህዋ አካሉ ሳይንሳዊ መለያ ቁጥሩ ኤችዲ 16175 እና ኤችዲ 15175ቢ የተሰኘው የኮከብና ኮኮቧን የምትዞር ፕላኔትን የያዘ ስርዓት ነው ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዜጎች 920 ላይ ስያሜውን በስልክ ጽሑፍ መልዕክት በመላክ ዜጎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስያሜውን እንድትሰይም ዕድሉ የሰጣት የዓለም አቀፉ የህዋ ህብረት አባል የሆነችው በቅርቡ መሆኑም ተገልጿል።