በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ የፈጠራ ሥራ ሽልማት ይፋ ሊደረግ ነው

በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያን የትምህርት ተቋማት ያሉበትን ደረጃ ለህዝቡ መረጃ ከማድረስ በበለጠ የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችን እውቅና ሽልማት በመስጠት ለስራዎቻቸው የበለጠ እንዲነሳሱ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ አዋቶ ለዋልታ እንደተናገሩት ኤጀንሲው እንዳስታወቀው በቅርቡ በዘርፉ ላይ የተሰማሩና በፈጠራ የተሻለ ስራን የሰሩ ግለሰቦችና ተቋማትን እውቅና የሚሰጥበትን መድረክ ማዘጋጀቱን ታውቋል፡፡  

ኤጄንሲው የሀገሪቷ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ለኢኮኖሚው እድገት የሚኖረዉን ሚና ከፍ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡

ምክትል ዳይሬክተሩ አክለዉ እንዳሉት የሀገሪቷ የቴክኒክና ሙያን የትምህርት ተቃማት ያለበትን ደረጃ ለህዝቡ መረጃ ከማድረስ የበለጠ የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችን እውቅና ሽልማት በመስጠት ለስራዎቻቸው የበለጠ እንዲነሳሱ ይረዳል ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ይህ መድረክ ለመጀመሪያ ግዜ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም አሰራር ተጠናክሮ የሚቀጥለብት ሁኔታ ላይ ኤጄንሲያቸው እየሠራ መሆኑን ምክትል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ በዋናነት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊው እንቅስቃሴ የተሻለ ስራ ሊያበረክቱ የሚችሉ እንዲሁም ወቀቅቱን የጠበቀ መሆኑ ይበልጥ ለተሳታፊ የሚያበረታታ ይሆናል ተብሏል፡፡

በመሆኑም በመላው ሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የፈጠራ ባለሙያዎች በኮንስትራክሽን፣ በግብርና፣ በኤሌክትሪካል በመካኒካል አገልግሎት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡