የህፃናት ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ቢሰጠውም ችግሩን መፍታት እንዳልተቻለ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በፖሊሲ የተደገፈ ሥራ ብታከናውንም ከችግሩ ስፋት አንፃር የህፃናት ደህንነት ችግርን መፍታት እንዳልተቻለ ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆየው 8ኛው አለም አቀፍ የህፃናት ፖሊሲ ጉባኤ በአዲስ አባባ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

"የህጻናት ርሃብ በአፍሪካ" በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን ኮንፈረንስ የከፈቱት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ እንዳሉት ባለፉት አመታት በተደረጉት ጥረቶች በረሃብ የሚጠቁ ህጻናት ሁኔታ የአህጉሪቱ አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡

በዚህም የህጻናቱን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ የተቻለ ቢሆንም፣ ብዙ መስራት እንደሚገባ ነው ፕሬዝዳንቷ ያሳሰቡት፡፡

በርሃብ የሚጠቁ ህጻናት ያሉበት ሁኔታ የሞራልና የፓለቲካ ጉዳይ መሆኑንና በሁሉም ደረጃ የሚገኘውን ማህበረሰብ ማንቀሳቀስና የሂደቱ አካል ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡