ምክትል ከንቲባ ታከለ የ10ኛ ክፍል ፈተና ሂደትን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የ10ኛ ክፍል ፈተና ሂደትን ጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በ81 የመፈተኛ ጣቢያዎች 57 ሺህ 447 ተፈታኞች ፈተናውን እየወሰዱ የሚገኙ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።/የከንቲባ ጽ/ቤት/