በአክሱም ሀውልት እድሳት ዙሪያ ለመምከር የጣሊያን ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል

የአክሱም ሀውልት እድሳት ዙሪያ ለመምከር በጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገለፀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አርቱሮ ሉዚ ጋር የአክሱም ሀውልት የእድሳት ስራ ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና የቤልትና ሮድ ጉባኤ ጎን ለጎን ከጣሊያኑ አቻቸው ጁሴፔ ኮንቴ ጋር በተወያዩበት ወቅት የአክሱም ሐውልትን ለማደሻ የሚውል እርዳታ ከጣሊያን መንግስት ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአክሱም ሀውልት ጉብኝት ማድረጋቸው እና ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዩ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡