በህብረተሰቡ ዉስጥ ያሉና በጥቅም ላይ ያልዋሉ ዕዉቀቶችን በምርምር ማዉጣትና መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ

በህብረተሰቡ ዉስጥ ያሉና በጥቅም ላይ ያልዋሉ ዕዉቀቶችንና ክህሎቶቸን በምርምርና ጥናት ማዉጣትና በጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አመለከቱ፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የእዉቀት ሽግግርን ጨምሮ ጥናትና ምርምሮችን ቢያካሂዱም በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ዙሪያ እየሰሩ ያሉት ስራ ግን በቂ እንዳልሆነ ምሁራኑ ገልጸዋል።

በመሆኑም ችግሮችን ለመቅረፍ ዘርፉን የሚመለከት የፖሊሲና የማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በባህር ዳር እየተካሄደ ባለዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና ምሁራን  የጋራ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዉ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ መንግስት በዉይይቱ የተነሱ ጉዳዮችን በቀጣይነት እንደሚመለከት ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትር ደኤታዉ በአዳጊ ክልሎች ያለዉን የትምህርት ስረዓት ማሻሻልና ማጠናከር ከቀጣይ የመግስት ትኩረቶች አንዱ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡