የባህል እሴቶችን ለሀገራዊ እድገት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ

የባህል እሴቶችን በመጠበቅ ለሰላምና እና መረጋጋትት እንዲሁም ለሀገራዊ እድገት የሚኖራቸውን ሚና በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ዛሬ በጅማ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያ የባህል ሳምንት በዓል ላይ ተገለፀ፡፡   

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ባህሉ ከሲምፖዚየም ባለፈ ለአዲስቷ ኢትዮጵያ የለዉጥ እና የብለፅግና ሂደት ላይ ትገኛለች ይህንን ለማስቀጠል ባህል መጠበቅ መንከባከብ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዋቅጋሪ ባህል የሰዉ ልጆች የማንነት መገለጫ በመሆኑ ባህሎቻችን በመጤ ባሕል እንዳይመረዙ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ ነገር ግን በቂ ባለመሆኑ የትምህርት ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት እና ሌሎች የድርሻዎች ሊወጡ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡

ዋልታ ያነጋገራቸዉ የባህሉ ተሳታፊዎች የባህል እሴቶቻችን ሰላም ለሀገራችን እድገት መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ባህል ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ እና ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡