ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ከፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጋር ዛሬ ይወያያሉ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት 400 ከሚሆኑ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጋር ይወያያሉ፡፡

ከውይይቱም በተጨማሪ በቤተመንግስቱ የጉብኝት ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወሰ ሲሆን፣ የተደረጉት ውይይቶችም ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ እንደ ነበራቸውም ተጠቁሟል።

ወደፊትም ተመሳሳይ ውይይቶች እንደሚቀጥሉም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡