2ኛው የሰዉ ሰራሽ አሰተዉሎት አዉደ ጥናት እየተካሄደ ነዉ

ሰዉ ሰራሽ አሰተዉሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሚመለከት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የተሳተፉበት ባለድርሻ አካላት ሁለተኛ አዉደ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ተገለፀ፡፡

በዋናነት ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ማዕከል ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ጋር በመተባበር ነዉ፡፡

በመድረኩ የተገኙት የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ ትሩፋቶች ተጠቃሚ እንድትሆን በተቀናጀ መልኩ መሰራት ይገባል ብለዋል፡፡ 

በአለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት መካከል አንዱ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት መሆኑን አረድተዋል፡፡

አዉደ ጥናቱ እነዚህ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በመዳሰስ ኢትዮጵያ በቀጣይ የፓሊሲ አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በትምህርቱ ዘርፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን የማቀለጠፍን እና ጥራት ያለዉ ትምህርት ተደራሽነት ለማሳደግ የቴክኖሎጂዉ ሚና የጎላ በመሆኑ የትምህርት ጥራትና የምርምር ተቋማት በዚህ ረገድ የበኩላቸዉ ድርሻ እንደሚወጡ አስገንዝበዋል፡፡

ይህም አዉደ ጥናት ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል ተብሏል፡፡