በመስቀል አደባባይ ብዙሃንን ያሳተፈ ስፖርት ተካሄደ

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ብዙሀንን ያሳተፈ የስፖርት መርሀ ግብር ዛሬ ተካሄደ፡፡

በመርሀ ግብሩን ያስጀመሩት የፌራደል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንደሻዉ ጣሰዉ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊየርጊስ እና የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳዉ ናቸዉ፡፡

ኮሚሽነር እነዳሻዉ እንደተናገሩት ይሄ ጅምር ስለሆነ እንጅ በየቀኑ መደረግ ያለበት ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡

የብዙሀን ስፖርት በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች መስፋፋት እንደሚገባዉ የተናገሩት ደግሞ የኢትጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊየርጊስ ናቸዉ፡፡

በአዲስ  አበባ የብዙን ስፖርት ከማስፋፋት ባሻገር  በከተማዋ ባሉት 116 ወረዳዎች  የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎች በመገንባት ላይ እናዳሉ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ገልፀዋል፡፡

እንደ ምክትል ከንቲባ ገለፃ በመሰራት ላይ ካሉት 60 ዎቹ  ተጠናቀዋል፡፡

ኮሚሽነር ርስቱ በበኩላቸዉ  የብዙሀን ስፖርት የጋራ ሀገራዊ አጀንዳ ለመቅረፅና ለሰላም ጣቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡