የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች በተለያዩ ቦታዎች ችግኞች ተከሉ

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት የተለያዩ ቦታዎች ችግኞች መትከላቸው ተገለጸ፡፡

የባለስልጣኑ ሰራተኞች ከ600 በላይ ችግኞችን የተከሉት በኮተቤ፣ በቃሊቲ ማሰልጠኛ እና በክፍያ መንገዶች ነው፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ የተተከሉ ችግኞችን የማፅደቅ ስራ በኃላፊነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ችግኞቹ የአየር ብክለትን በመከላከል ረገድ ባለስልጣሉ ከሚያከናውናቸው የትራንስፖርት ተግባራት በተጓዳኝ ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸዉ  ዳይሬክተሩ አክለዉ ገልፀዋል፡፡