የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልድያ/ሃራገበያ የባቡር ፕሮጀክት ሰራተኞች 50ሺ ችግኞችን ተከሉ

የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልድያ/ሃራገበያ የባቡር ፕሮጀክት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች የባቡር መስመሩ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የችግኝ ተከላ አከናወኑ፡፡

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ በዘንድረው ዓመት መርሃ ግብር ከአዋሽ እስከ ሃራ ገበያ ባለሉ የባቡር ጣቢያዎች፣ በወርክ ሾፕና በትራክሽን ሰብስቴሽኖች ከ370ሺ በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።

በአሁኑ መርሃ ግብርም በመስመሩ ባሉ ባቡር ጣቢያዎች ከ50ሺ በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

በመርሃ ግብሩ እያንዳንዱ የፕሮጀክቱ ሰራተኛ እንዲሳተፍ እየተደረገ ሲሆን፤ ሰራተኛው የተተከሉ ችግኞች ክትትል የሚያደርጉበት አሰራርም መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ መረጃው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን አገልገሎት ነው።