የአድዋ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር እና የታሪካዊ ድሉን ሁለንተናዊ ይዘት ለትውልድ ለማሻገር ሊገነባ የታሰበው የአድዋ ማዕከል በዛሬው ዕለት ግንባታው ተጀምሯል፡፡

የአድዋ ማዕከል ግንባታ ለረዥም ጊዜያት ሳይለማ በቆየው እና ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ግንባታው ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል በተባለ አለም አቀፍ ኩባንያ የሚካሄደው የአድዋ ማዕከል በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ በውስጡ "ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!" የሚል የአዲስ አበባ ከተማ 'ዜሮ (0.00) ኪ.ሜ' ምልክት ያርፍበታልም ተብሏል መረጃዉ የከንቲባ ጽ/ቤት ነዉ ፡፡