የአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 30 ይካሄዳል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት ከትምህርት ሴክተር ከተውጣጡ አመራሮች እና ባለሞያዎች ጋር በክረምት ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም ለማቅረብ እና የምገባ መርሃ-ግብር ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እና የምገባ አገልግሎት የሚያገኙ ተማሪዎችን ትክክለኛ መረጃ ለመሰብሰብ ሲባል ምዝገባው ቀደም ብሎ ማለትም ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 30 እንደሚካሄድ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት በመንግስት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

(ምንጭ፡-የከንቲባ ጽህፈት ቤት)