ጠ/ሚ ዐቢይ ለ2019ኙ የቻታም ሀውስ ሽልማት መታጨታቸውን ተቋሙ አስታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለ2019ኙ የቻታም ሀውስ ሽልማት መታጨታቸውን ተቋሙ ይፋ አድርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሽልማቱ የታጩት አሳታፊ ፖለቲካንና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በኢትዮጵያ በማምጣታቸው መሆኑን ቻታም ሀውስ ገልጿል፡፡

ታሪካዊው የኢትዮ-ኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት እውን ይሆን ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጫወቱት ቁል ሚናም በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ከወሰዱት ገንቢ እርምጃ በተጨማሪ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ውህደት የፈነጠቁት ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለሽልማቱ እንዳሳጫቸው ቻታም ሀውስ ገልጿል፡፡