የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ 7ሺህ 475 ተማሪዎችን አስመረቀ

የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ 7ሺህ 475 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 146 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 2ሺህ 275 በሁለተኛ ዲግሪ እና አራት ተማሪዎችን በሦስተኛ ዲግሪ ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግገር ተማሪዎች ለምረቃ የበቁት በክልሉ ሰላም በመኖሩ መሆኑን በመግለጽ፤ ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን ለተመራቂ ተማሪዎች አስገንዝበዋል።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲም የክልሉ መንግስት በሚያደርገው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ በተለያዩ ምርምሮች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 418 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰአት ከ33 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ተገልጿል።