177 ችግኞችን የነቀለው ግለሰብ በ6 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በምእራብ አርሲ ዞን ሄበን ወረዳ 177 ችግኞችን የነቀለው ግለሰብ በስድስት አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡

በምእራብ አርሲ ዞን የሄበን ወረዳ ፍርድ ቤት ሃምሌ 12፣ 2011 በዋለው ችሎት በሄበን አርሲ ወረዳ ደጋጋ ቀበሌ 177 ችግኞችን ሲነቅል እጅ ከፍንጅ የተያዘውን ግለሰብ ፋይል ተመልክቷል፡፡

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የሙኔሳ ወረዳው ነዋሪ የሆነውን አቶ ትቤሶ ያበቱ ሃምሌ 9፣ 2011 ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ በሙኔሳ ዲስትሪክት የመንግስት ደን ውስጥ በዚህ ክረምት ከተተከሉ ችግኞች መካከል 177 ችግኞችን በመንቀል በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

በዚህም በተከሳሹ ላይ የስድስት ዓመት ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ችግኞቹ 3 ሺህ 640 ብር ግምት እንዳላቸውም ነው የተገለጸው፡፡