ለአካባቢ ንጽህና ጥበቃና ወንጀልን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – የኮተቤ አካባቢ ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ የኮተቤ አካባቢ ወጣቶችና ነዋሪዎች ለአካባቢ ንጽህና ጥበቃና ወንጀልን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠየቁ፡፡

በአካባቢያቸው በሞተር ብስክሌት የታገዘ ዝርፊያና ንጥቂያ ሲፈፀም እንደነበር ገልጸው፣ ወጣቶቹና ነዋሪዎች በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ከጀመሩ ወዲህ ግን የወንጀል ድርጊቱ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ብለዋል፡፡

ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የወንጀል መከላከልና የጽዳት ዘመቻው በየወሩ መርሃ ግብር ወጥቶለት እንደሚከናወንም ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ይህን ተግባር ቢያከናውኑ መልካም እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በመጪው ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም ለሚደረገው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡