የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአካባቢ ጥበቃ ሥራ አርአያ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአቅራቢያቸው ለሚገኙ ማህረሰቦች በአካባቢ ጥበቃ ሥራ አርአያ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ፡፡

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አለሙ ስሜ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከምርምር ሥራዎች ባሻገር በአከባቢ ጥበቃ ሥራ በአቅራቢያቸው ላሉ ነዋሪዎች አርአያ መሆን መቻል አለባቸው ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አመራር አካላት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቦችና የከተማዋ ነዋሪዎች የችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡

ከወራቤ ከተማ በቅርብ ርቀት የተገነባው ዩኒቨርሲቲውን አረንጓዴ ለማድረግ የተቋሙ ቦርድ አመራሮችና ማህበረሰቦች በአንድ ወር ብቻ ከ26ሺህ በላይ ችግኞች ተክለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቶፊክ ጀማል በበኩላቸው በሰው ልጆች ሚዛኗን እየሳተች ያለችው አለምን መታደግ ይገባል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጪው ሃምሌ 22 ሃገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 3 ሺህ ችግኞችን በቅጥር ግቢው ለመትከል መዘጋጀቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን 3ሺህ ተማሪዎች አሉት፡፡