የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መዘጋጀታቸውን ገለፁ

ሀምሌ 22፣ 2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ ዝግጅት እያደረጉ መሆናውን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ  እኛ ያጠፋነውን እኛው መመለስ አለብን በማለት ችግኖቹን ለመትከል ብቻም ሳይሆን ለመንከባከብ ዝግጁ መሆናቸውም ነው ለዋልታ የተናገሩት።

ተቋማት በበኩላቸው ለጉዳዩ ትኩረት በመቸርና በጀት በመመደብ ለችግኝ ተከላ ቋሚ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡

በቀጣይ ሀምሌ 22፣ 2011 ዓ.ም በሚካሄደው ብሄራዊ  ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ -ግብር ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውንም  ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡