የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ወረርሽኙ  እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ

የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ወረርሽኙ  እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ

በዘንድሮ ዓመት የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ወረርሽኙ  እየቀነሰ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዘንድሮ ዓመት የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ወረርሽኙ  እየቀነሰ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዘንድሮ የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ በሽታውን ለመቆጣጠር የመስኖና ኢነርጂና ዓለምአቀፍ ተቋማትን በማሳተፍ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2030 ኮሌራን ለማጥፋት ዓለም አቀፍ ዕቅድ ለኢትዮጵያ በሚመች ሁኔታ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡  

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍ የሚሰጥ የኮሌራ ክትባትና ሌሎች ድጋፎችን እያረገ መሆኑንና በዘላቂነት ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡

የ10 ዓመታት ዕቅዱን ለመሳሳካት የሚያስችል ውይይት በአውሮፓ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ከዓለም ጤና ድርጅት የመወያያ ርዕስ ያነሱት ዶክተር ዶሚኒክ ሌብሮስ፤ የኮሌራ በሽታ በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚያጠቃ ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በ20 የዓለም አገሮች ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ በሽታ መቆጣጠር መቻሉን ዶክተር ዶሚኒክ አክለው አስረድተዋል፡፡ ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በሽታውን መቆጣጠር እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው፤ የገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ እየታየ ያለው የውሃ ወለድ በሽታን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የህብረተሰቡን ንጽህና አጠባባቅን በተመለከተ የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡  

በዓለም ላይ ከሚያዚያ 2017 እስከ 2018 ድረስ አንድ ሚሊየን፣ 90ሺህ፣ 280 ሰዎች በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሲሆን፣ 2ሺህ 275 ያህሉ ሞታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡