የእነ አቶ አብዲ መሀመድ የክስ  መዝገብ  እንዲሻሻል ብይን ተሰጠ

በእነ አቶ አብዲ መሀመድ የክስ  መዝገብ  የአቶ አብዲ መሀመድ እና ዘምዘም ሀሰን ክስ እንዲሻሻል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ብይን ሰጠ፡፡

የሌሎቹን ተከሳሾች መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው ችሎቱ፤ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ተቀብሏል፡፡

ተከሳሾቹ  ድርጊቱን አልፈጸምንም ሲሉ  ክደው በመከራከራቸው አቃቤ ህግ ምስክሮቹ እንዲሰሙለት አመልክቷል፡፡

ፍርድቤቱ ባለፈው ሳምንት መቃወሚያ ባስገቡ ተከሳሾች ጉዳይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፤ የችሎቱ አንድ ዳኛ በእክል ምክንያት በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ብይኑን ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡