በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 353,633,660 ችግኞች ተተከሉ
በኢትዮጵያ ሐምሌ 22/2011 በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በመላ ሃገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች መተከላቸው ተረጋግጧል።
በአገሪቷ በአረንጓዴ አሻራ ቀን 200ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ በተደረገው ዘመቻ በአንድ ጀምበር በመላ ሀገሪቱ 353 ሚሊየን 633 ሺህ 660 ችግኞች ተተክሏል። ይህም በህንድ ከዚህ ቀደም ተይዞ ከነበረው የ66 ሚሊየን ችግኝ በእጅጉ የላቀ መሆኑ ተረጋግጧል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ፤ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድርና ከንቲባዎች፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ችግኝ ተክለዋል። በዘመቻው መላው የአገሪቱ ህዝብ አንድ ሆኖ ሲሳተፍ ተስተውሏል።