የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከጃፓን መንግስት የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጃፓን መንግስት የክብር ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ሽልማቱ የ2019 ስፕሪንግ ኢምፔርያል ሽልማት ሲሰኝ በጃፓን መንግስት በኩል የተለየ ተግባር ላከናወኑ የውጭ ሀገራት መሪዎች የሚሰጥ ነው፡፡

ሽልማቱን የሰጡት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኬ ማትሱናጋ ናቸው፡፡

በተለይም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ዘመናቸው በኢትዮጵያ ተፈጥሮ የነበረውን ማህበራዊ ቀውስ እልባት ለመስጠት ላበረከቱት አስተዋፅኦ፣ በጤናው ዘርፍ እና የካይዘን ፍልስፍናን በማስረፅ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ለነበራቸውን አስተዋፅኦ የተበርከተ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት ለማርገብ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን አቶ ኃለማርያም ከሽልማቱ በኋላ ተናግረዋል፡፡