የኦሮሞና የሱማሌ ሕዝቦች የምክክር መድረክ ተጀመረ

የኦሮሞና የሱማሌ ህዝቦች የወንድማማችነት የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ዑመር፣ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሁለቱ ክልል ህዝቦች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ በሚያዚያ ወር ላይ በአዳማ ከተማ የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።

(ምንጭ፡-  ኢቢሲ)