በኦሮሚያ ክልል ምክትል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ በዛሬው ዕለት በሱማሌ ክልል ደገሃቡር እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝት ስነ ስርዓቱ ላይ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ተሳታፊ ሆነዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የህዝብ ለህዝብ መድረኩ በዋና ከተሞች ብቻ ሳይሆን እስከ ታች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን ለማሳየት እንደሆነም ነው የተገለፀው።
የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልሎች ህዝቦችን ግንኙነት የሚያጠናክር የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ በትናንትናው ዕለት መካሄዱ ይታወሳል።
በምክክር መድረኩ ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ ከ750 በላይ ከሁለቱም ክልሎች ሁሉም ዞኖች የተወጣጡ ልኡካን መሳተፋቸውን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል።