የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለ50 ቀናት በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ተገለጸ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለ50 ቀናት በከፊል ዝግ ይሆናሉ።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሃሴ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው 50 ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ፣ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች ግን እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡

የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች ፍርድ ቤቶቹ ዝግ ቢሆኑም ይታያሉ ነው የተባለው።

ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮችም በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በላከው መረጃ መሰረት።