ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕሬህን ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልማት ትብብር ሚኒስትሩ በኢነርጂ ፖሊሲ፣ ስራ ፈጠራ፣ ኢንቨስትመንት፣ ዴሞክራሲ፣ የአየር ለውጥና አከባቢ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተገኘው መረጃ መሰረት።