መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ የመንግሥት እና የባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የሙከራ ምዕራፍ ትግበራን አስመልክቶ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ በሸራተን ሆቴል ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የመቀንጨር ችግርን በሚፈለገው ደረጃ ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ የሰቆጣ ቃልኪዳን አፈፃፀም ላይ የሚታዩ የበጀት፣ የግብዓት እና ተያያዥ ችግሮችን በመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል። (ምንጭ፡-የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት)