በደቡብ አፍሪካ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ የማድረጉ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁ የማድረጉ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከተማ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የውጭ አገራት ዜጎች በሚነግዱበት የቢዝነስ ሴንተር ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ አለ በሚል አለመግባባት በአገሪቱ ህግ አካላት መታሰራቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያውያኑን ለማስለቀቅ በፕሪቶሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በዚያው በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የአትዮጵያ ኤምባሲ ማህረሰብ ከአመራሮች ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያኑ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው እና በህጋዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ከእስሩ እንዲፈቱ የማድረጉ ስራ መኖሩን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በሱዳን በኩል ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ኢትዮጵያ እና እና የአፍሪካ ህብረት ለመፍታት ላሳዩት ቁርጠኝነት እውቅና መገኘቱን አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም እየተሰራበት እንደሆነ ገልጸው፣ በመካከለኛው ምስራቅ ስራ ሰርተው ደሞዝ የተከለከሉ ዜጎች ደሞዝ እንዲከፈላቸው የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በእስር ቤት የነበሩ ዜጎች ከከእስር ተለቀው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስራቱን ገልጸው፣ በኬንያ ታስረው የነበሩ 64 ኢትዮጵያውያን በኢፌዴሪ በኬንያ ኤምባሲ በኩል መፈታታቸው አስታውሰዋል፡፡