የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማዋ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማ አስተዳደሩና በባለሀብቱ እየታደሱ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 488 የመንግስት ትምህርት ቤቶች እየታደሱ የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን ወደ መጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡

የትምህርት ቤቶቹ እድሳት ለተሻለ መማር ማስተማር እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ለተማሪዎችም ሆነ ለአስተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

ከእድሳት እና ጥገና ስራዎች በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በየትምህርት ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተማሪዎች የአረንጓዴ ቦታ እና ምቹ የመመገቢያ አዳራሾች በአዲስ መልክ የሚደራጁ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ምክትል ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት በየትምህርት ቤቶቹ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ጋርም ቆይታ አድርገዋል፡፡

ከንቲባው በዛሬ ጉብኝታቸው በአስሩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች እድሳት ሂዴትን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡