በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው

የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ በአሶሳ እየተካሄደ ነው::

የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአማራ፣የኦሮሚያና የጋምቤላ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መድረክ ሲሆን፤ የክልሎቹ አፈ ጉባኤዎች፣ የቢሮዎች ሀላፊዎች፣ እንዲሁም የአራቱ ክልሎች ተጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች አመራሮች በመታደም ላይ ናቸው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከኦሮሚያ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የጋራ የሰላምና ልማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በትብብር መድረኩን አዘጋጅተዋል፡፡

ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው የምዕራብ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ሁኔታ፤ ፌዴራሊዝምና የሰላም እሴት ግንባታ፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝና የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ ልማትና ሰላም ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡