ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ በዋግ ኽምራ ያስገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የቀድሞውን የዳስ ትምህርት ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስገንብቶ አስመርቋል፡፡

አትሌቱ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ ላይ ያስገነባው ገልኩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ለምረቃ የበቃው፡፡

ትምህርት ቤቱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተሰኝቷል፡፡

ሁለት ብሎኮችና ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ያሉትን ይህን ት/ቤት ኃይሌ በሦስት ወራት በማስገንባት ነው ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ማስተማሪያ ዝግጁ ያደረገው፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ  ነዋሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንድ ግለሰብ 8 ሺህ 500 የማጣቀሻ መጻህፍትን ለትምህርት ቤቱ መለገሳቸው ተገልጿል፡፡