ከተማ አስተዳደሩ ጳጉሜ 3 ቀን ለሚከበረዉ “የሀገራዊ የኩራት ቀን” ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 3 ቀን የሚከበረዉን  "የሀገራዊ የኩራት ቀን" ለማስተባበር ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናገረ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፌቨን ተሾመ አንደተናገሩት  መርሀ-ግብሩ የተለያዩ ሀገራዊ እሴቶችን ይበልጥ በሚያጎሉ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ 250 ሺህ ሰዎች የሚታደሙ ሲሆን በዕለቱ የመከላከያ ሰራዊት አየር ኃይል ወታደራዊ ትርኢት ያደርጋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችም የተለያዩ ትርኢቶችን እንደሚያሳዩ የገለፁት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ የኢትዮጵያን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሰችን የማስተዋወቅ ስራም ይኖራል ብለዋል፡፡

በዕለቱ “አዲስ አበባ ቤቴ፤ ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ” የሚል ፁሁፍ የተፃፈበት 100 ሺህ ቲሸርት በነፃ ለታዳሚዎች ይከፋፈላል፡፡

ዝግጅቱ በመስቀል አደባባይና በሚለኒየም አዳራሽ ይከበራል ተብሏል፡፡