ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶክተር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ደቡብ ኮሪያ ሴዑል ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው ሴዑል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ወዳጆችና በዚያው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በሴዑል በሚኖራቸው ቆይታም ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን ጋር በሀገራቱ መካከል ስላለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታላላቅ የሀገሪቱን ኩባንያዎችንም ይጎበኛሉ።