የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በመጪው እሁድ ይካሄዳል

ለአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን በአዲስ አበባ የትግራይ ሴቶች ማህበር አስታውቋል፡፡

የማጠቃለያ ዝግጅቱ  በሚሊኒየም አዳራሽ ነሃሴ 26፣ 2011 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡

በዝግጅቱ ላይ አምባሳደሮች ፣ከመላው ብሄር፣ ብሄረሰቦች የተወከሉ ግለሰቦችና አመራሮችን ጨምሮ  ከ30 ሺህ በላይ ሴቶች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡

አዘጋጆቹ የአሸንዳ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) እንዲመዘገብ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን  ለዋልታ ቴሌቭዥን ገልፀዋል፡፡

የአሸንዳ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከትውልድ  ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግም  ይሰራል ብለዋል፡፡