በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ የተጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

በእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ይግባኝ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል፡፡

የባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቂ የምርመራ ጊዜ መሰጠት አለመሰጠቱን ለማጣራት በዳኞች አብላጫ ድምፅ ይግባኝ ቀርቧል፡፡

ዐቃቤ ህግ በአራት እና አምስት ጊዜ ቀጠሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ባለማቅረቡ ነው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ይግባኙ ውድቅ የተደረገው፡፡

ዐቃቤ ህግ ይግባኝ የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በትናትናው ዕለት የእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የቀዳሚው ምርመራ መዝገብ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

(ዘገባው የአብመድ ነው፡፡)