ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች እያስረከበ መሆኑን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች እያስረከበ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረገላቸውን ቤቶች ለአረጋዊያን እና አቅመ ደካሞች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለትም mክትል ከንቲባው እድሳቱን ያስጀመሩትን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቃኘው ሻለቃ ተብሎ በሚጠራው አደባባይ አከባቢ የሚኖሩ እናት መኖሪያ ቤት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ለባለንብረቷ ቤታቸውን ማስረከባቸወን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር 1 ሺህ ለሚሆኑ አረጋዊያን ቤት ለማደስ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፣

እስከ አሁን 1 ሺህ 573 ለሚሆኑ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከዚህም ውስጥ 1 ሺህ 111 ቤቶች እድሳት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለባለንብረቶቹ መተላፉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡