20ኛው የአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በደብረብርሃን እየተካሄደ ነው

በ2012 የመማር ማስተማር ሂዴት ላይ ትኩረት ያደረገው በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 20ኛውን ፎረም በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በፎረሙ በክልሉ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የቦርድ አመራሮች፣ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተማሪ መማክርትና አባላት ተገኝቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የመማር ማስተማር ሂደቶች፣ የምርምርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት፣ የአስተዳደር ጉዳዮችና የተማሪዎች ህብረት የ2012 ዓ.ም ዕቅዶች ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የአማራ ክልል የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረሙ የክልሉን ቢሎም የሀገሪቱን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመደገፍ ረገድ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ በመድረኩ ላይ ተነስተዋል፡፡

በመድረኩ በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና የተሞክሮ ልውውጥ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደምፈጥር ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌጉባኤ ወይዘሮ ትልቅሰው ይታያል ፎረሙ የክልሉን ሁሉንአቀፍ እንቅስቃሴ በማገዝ ረገድ አበረታች ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ለፎረሙ ዕቅዶች መሳካት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡