ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንድትችል መንግስት በትኩረት ይሰራል

ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም ማግኘት እንድትችል መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
የቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ በሀገራዊ እደገት የሚኖረውን ድርሻ ማሳደግ እና የስራ እድል ፈጠራን በማበረታታት ድራሻው የላቀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ አገሪቷ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲትሆን መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ጠ/ር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

ይህ የተገለጸው በአንደኛው ሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ላይ ሲሆን፤ ኮንፈረንሱ አንደኛው ሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ቱሪዝም ብሩህ ተስፋ ለየኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በጀመረበት ወቅት ነው፡፡

ምድረ ቀደምት የሚል ስያሜ የተሰጠው የቱሪዝም ዘርፍ ያሉበት ውስንነቶች እንዳሉ ሆኖ፤ ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ እያበረከተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ለ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ 10 አይነት የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ያቀፈችና 11 ቅርሶችን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ሳይንስና ባህል ተቋም ያስመዘገበች ቢሆንም፤ የተመገቡ ብሎም በመመዝገብ ሂደት ላይ ያሉ የማይዳሰሱ ሀብቶች ቢኖሩም ጥራት ካለው አግልግሎት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ማነቆ አበርክቶውን ውስን አድርጎታልልም ነው የተባለው፡፡

በኮንፈረንሱም በጥናት የተለዩ ክፍተቶችን በማቃለል ወደ እድል በመቀየር ሂደት መንግስትና የግሉ ባለሀብት የጎላ ሚና እንዳላቸው መመላከቱን ተከትሎ መንግስት በዘርፉ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የኢፌዲሪ ምክትል ጠ/ር ደመቀ መኮንን በመክፈቻ ሰነ-ስረዓቱ ላይ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ኢትዮጵያ እንግዳ መቀበል ቀደምት ሀገራዊ ባህሏ መሆኑን በመጥቀስ፤ የአገሪቷን እምቅ ሀብቶችን ዓለም ከደረሰበት ደረጃ አስተሳስሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽኖት በመስጠት አሳስበዋል፡፡

ከመድረኩ መንግስትም ሆነ የግሉ ዘርፍ ተሞክሮ የሚሆኑ ግበዓቶችን የሚወስዱበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡