መንግስት ቤተክርስቲያኗ በየጊዜው ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ባለመስጠቱ ለተደራራቢ ችግር መዳረጓ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በየጊዜው ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ቤተክርስቲያኗ ለተደራራቢ ችግሮች መዳረጓ ተገለጸ፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከብሯል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በተከበረበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ቤተክርስቲያኗ ለተደራራቢ ችግሮች መዳረጓ ተገልጿል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የገጠማትን ወቅታዊ ፈተና ለማለፍ ዋናው መንገድ መንግስት የሀገርንና የቤተክርስያኗን ሰላም ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና፣ በመቀራረና በመነጋጋር የተዘጋጀውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር ቤተክርስቲያኗን በክብር ጠብቆ በማስቀጠል ለትውልድ ማስተላለፍ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመለክቷል፡፡

የብፁዕነታቸው በዓለ ሲመት ሲከበር፤ ብፁዕነታቸው በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቤክርስቲያኗ ቀደም ሲል የነበሩባትን ችግሮች ወደ ጎን በመተው በእርቀሰላምና ሲኖዶሳዊ አንድነት ለበዓለ ሲመታቸው በመድረሳቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል። ምዕመናን ከሚፈታተናቸው ግላዊ ፍላጎት በመታቀብ በአንድነት ለሀገርና ለቤተክርስቲያኗ ዕድገት በመትጋት ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት ይገባልም ብለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው በዓለ ሲመታቸውን ለማክበር የታሰበውን አንድ ሚሊዮን ብር በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተክርስቲያናት ማሰሪያ እንዲውል አድርገዋል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ነሐሴ 29 ቀን 1980 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡