ጠ/ሚ ዐቢይ በቻይና ነፃ የትምህርት እድል ላገኙ 288 ተማሪዎች ሽኝት አደረጉላቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና ነፃ የትምህርት እድል ላገኙ ተማሪዎች በተዘጋጀ የመሸኛ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ሽኝት አደረጎላቸዋል፡፡

እነዚሁ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ መርሀግብር ለመሰልጠን የተመረጡ ተማሪዎች በቻይና የንግድ ሚኒስትር መሪነት ሀገሪቱ ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖራትን ተግባቦትና ትብብር ለማጠናከር ባቀደው ሞፍኮም በሚባለው የነፃ ትምህርት እድል የታቀፉ ናቸው::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና መንግስት ግለሰቦችን ለማስተማር የምታደርገውን ድጋፍ በማድነቅ ተማሪዎቹም በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ ድልድይ ሆነው እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል::

ተማሪዎቹም የኢትዮጵያን ችግሮች ለማቃለል ቁልፉ እውቀት መሆኑን በመገንዘብ ሲመለሱ ሀገራቸው ብዙ እንደምትጠብቅባቸው አስታውሰዋቸዋል::

ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠትና የነፃ ትምህርት እድሎችን በማመቻቸት ላይ ትገኛለች:: በሞፍኮም ፕሮግራም ከ800 በላይ ከሁሉም የፌዴራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና የክልል መንግስታት የተውጣጡ ባለሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን ወስደዋል::

በተጨማሪም እስከ አሁን ከ400 በላይ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በዚህ አመት ብቻ 228 ግለሰቦች የከፍተኛ ትምህርታቸውን በቻይና ለመከታተል እድል አግኝተዋል:: መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው፡፡