አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 87 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 87 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ እንዳሉት አዲሱ አመት 2012ን ምክንያት በማድረግ  በይቅርታ  የሚለቀቁት ከሁሉም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች የተውጣጡ ታራሚዎች ናቸው ፡፡

በይቅርታ ከሚለቀቁት ውስጥ 439 ከሸዋሮቢት ፣ 367 ከቃሊቲ፣ 28ቱ ደግሞ ከዝዋይ  ማረሚያ ቤቶች  መሆናቸውንም ነው የገለፁት።

አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ የሚለቀቁ ታራሚዎች በህግ ይቅርታ የማይጠየቅባቸው ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው በማረሚያ ቤት የቆዩ መሆናቸውን የኤፍቢሲ ዘገባ  ያመለክታል።